ልጅ ቧያለው ጌታቸው አባተ

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ መስራችና ከቦርድ አባላት አንዱ የነበሩት እና የህይወት ዘመን አባል የሆኑት #ልጅ_ቧያለው_ጌታቸው_አባተ ባሳለፍነው ሳምንት ከባለቤታቸው #ወሮ_ማንያህልሻል_አንተነህ ጋር በመሆን ማዕከላችንን በመጎብኘት የሕይወት ማዳን ስራው እንዲቀጥል አሁንም አብረናችሁ ነን ብለውናል፡፡

ልጅ ቧያለው በጉብኝታቸው ወቅት በአያታቸው #ራስ_አባተ_ቧያለው_ንጉሡ (አባ ይትረፍ) ህይወት ዙሪያ የታተመውን መፅሐፍ ለማዕከላችን በስጦታ መልክ ያበረከቱ ሲሆን መፅሀፉ አባትና አያቶቻችን ሀገር ለመገንባትና ለእኛ ለማውረስ ያደረጉትን ጥረትና የከፈሉትን መስዋትነት የሚያሳይ በመሆኑ አሁን ያለው ትውልድ ትልቅ ትምህርት እንደሚያገኝበት ታሪኮችን በመጥቀስ አውግተውናል፡፡

ልጅ ቧያለው ከመፅሐፍቶቹ በተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍም ያደረጉ ሲሆን፤ ለማዕከላችን ዕውን መሆን እና ለበርካታ ሕፃናት ሕይወት መዳን ከመስራች አጋሮችዎ ጋር በመሆን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለንን አክብሮት እየገለፅን በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም ላደረጉልን ድጋፎች ከልብ እናመሰግናለን፡፡

#Cardiac_Center_Ethiopia
#6710_A_B_C_D

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *