አስኩ ኃላ.የተ.የግ.ማ (ASKU P.L.C.) ለልብ ማዕከል የመፅሀፍት ድጋፍ አደረገ

በአኳ አዲስ ምርቱ እና በተለያዩ ዘርፈ ብዙ የንግድ እንቅስቃሴዎች የሚታወቀው አስኩ ኃላ.የተ.የግ.ማ (ASKU P.L.C.) የልብ ሕሙማንን ለረጅም ዓመታት በተለያዩ መንገዶች ሲደግፍ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በማዕከላችን ውስጥ ለተቋቋመው ቤተ መፅሀፍት 306 መፅሀፍቶችን አበርክቷል፡፡

የቤተ መፅሀፍቱ መቋቋም የሕክምና ባለሞያዎች ለሚያደርጉት የዕውቀት ማዳበር እና ሽግግር፣ በማዕከሉ ሰራተኞች ዘንድ የንባብ ልምድን ለማዳበር እና በዋነኛነት በማዕከላችን ለሚታከሙ ሕፃናት የንባብ ጊዜን በመፍጠር ትልቅ ሚና የሚጫወት ይሆናል፡፡ አስኩ ኃላ.የተ.የግ.ማ ከጎናችን በመሆን ላደረገልን ድጋፎች እና ላበረከተልን የመፅሀፍት ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

ለቤተ መፅሀፍቱ የመፅሀፍት ድጋፎችን ለማድረግ ለምትሹ በ0977909090 ወይም 0115513636 ልታገኙን ትችላላችሁ፡፡

#ASKU_PLC | #ABIG_GROUP | #AQUAADDIS#CCE | #CHFE | #6710_A_B_C_D

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *