ኢትዮ ቴሌኮም እና የልብ ሕሙማን

የረጅም ጊዜ አጋራችን የሆነው #ኢትዮ_ቴሌኮም ዛሬም እንደሁልጊዜው የድጋፍ ጥሪያችንን ተቀብሎ አስተናግዶናል፡፡

ላለፉት በርካታ ዓመታት በተለያዩ መንገዶች ማዕከላችንን ለመደገፍ በሩን ክፍት አድርጎ የሚጠብቀን #ኢትዮ_ቴለኮም የ6710 ዓጭር የፅሁፍ መልዕክት በነፃ በመፍቀድ፣ የ30ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ስፖንሰር በማድረግ እንዲሁም ለሚያጋጥሙን የኮሚኒኬሽን ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ማዕከላችን ለሚያከናውናቸው የሕይወት ማዳን ስራዎች ትልቅ ሚና ተጫውቷል በመጫወት ላይም ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ማዕከላችንን ለሚያደርጋቸው የውጪ ግንኙነቶች፣ የህክምና ምርምሮች፣ የህዝብ ግንኙነት ስራዎች እና የሕክምና አስተዳደር መረጃ ስርዓት (Health Management Information System) የሚጠቀምበት የነፃ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ በመፍቀድ የተቀላጠፈ አሰራር እንዲፈጠር አድርጓል፡፡

በአሁኑ ወቅትም #ኢትዮ_ቴሌኮም የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ በመቀጠል ማዕከላችን እስከ መስከረም 2020 ድረስ የተጠቀመውን የብሮድባንድ ኢንተርኔት ወጪ ብር 652,979.94 እንዲሁም እስከ ሰኔ 2021 ድረስ የሚጠቀምበትን ወጪ ብር 215,690.40 በድምሩ ብር 868,670.34 በመፍቀድ ትልቅ ድጋፍ አድርጎልናል፡፡ወረፋ በመጠበቅ ላይ ለሚገኙ በርካታ ሕፃናት የምንሰጠውን የነፃ የልብ ቀዶ ጥገና አጠናክረን እንድንቀጥል #የኢትዮ_ቴሌኮም ሚና ትልቁን እና ዋነኛውን ቦታ ይይዛልና በታካሚ ሕፃናቱ ስም ያለንን አክብሮት እና ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን፡፡

#ethiotelecom | #ethiotelecomcsr | #chfe | #cce

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *