የረውማቲክ የልብ በሽታ እንዳይባባስ የሚረዳውን በመርፌ የሚሰጥ ህክምና (ቤንዛቲን ፔኒሲሊን)

በዶ/ር አዘነ ደሴ መንግስቱ በልብ ማዕከል የህፃናት የልብ ሐኪም

  1. የመርፌ ህክምናው የሚሰጠው በየስንት ጊዜ ነው?

በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን ባለው የህክምና አሰጣጥ ስርአት መሠረት የሪውማቲክ የልብ በሽታ ላለባቸው በሽታው እንዳይባባስ የሚረዳው የመርፌ ህክምና የሚሰጠው በወር አንድ ጊዜ ነው፡፡

  • የመርፌ ህክምናውን በየወሩ መውሰድ ያለባቸው እነማን ናቸው?

በሽታው መኖሩ በሐኪም የተረጋገጠ የሪውማቲክ የልብ በሽተኞች ሁሉ ይህ የመከላከያ መርፌ ያስፈልጋቸዋል፡፡

  • ለመሆኑ በኦፕራሲዎን ወይም ያለ ኦፕራሲዎን የልብ ህክምና የተደረገላቸው የሪውማቲክ የልብ ህሙማን በየወሩ የሚሰጠውን መርፌ መውሠድ ያስፈልጋልቸዋል?

በሪውማንቲክ የልብ በሽታ የተጎዳውን  የልብ ቫልቭ ለማስተካከል የሚደረገው ህክምና በድጋሜ ሪውማንቲክ የልብ በሽታ ቫልቩ እንዳይጎዳ የሚያደርግ ባለመሆኑ ችግሩ እንዳይባባስና የልብን አሰራር በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅ በየወሩ የሚሰጠው የመርፌ ህክምና (ቤንዛቲን ፔኒሲሊን) እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

  • የመርፌ ህክምናው የሚሠጠው የት ነው?

ህክምናው መሰጠት ያለበት በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች በጤና ድርጅት ነው፡፡

  • ቤንዛቲን ፔኒሲሊን የመርፌ ህክምናው የጎንዮሽ ችግር ምንድነው?

መርፌውን ከሚወስዱ አንድ ሺ ሰዎች መካከል በአንዱ ሰው ላይ ሊከሰት ከሚችል የአለርጂ ችግር ውጭ ህክምናው አሳሳቢ የሆነ የጎንዮሽ ችግር የለውም፡፡

  • በየወሩ የሚሰጠውን የቤንዛቲን ፔኒሲሊን ህክምና የቀጠሮ ጊዜ ለማስታወስ ምን ማድረግ ይቻላል?
  • በስልክ (በሞባይል) አስታዋሽ መልክት ማስቀመጥ
  • በግል ካሌንደርዎ ምልክት ማስቀመጥ
  • በጤና ድርጅት የሚሠጥዎን የቀጠሮ ካርድ መጠቀም
  • ሊያስታውስዎ ለሚችል ሰው በየወሩ የህክምና ቀጠሮ እንዳለዎት ማሳወቅ
  • ሌሎች ለያስታውስዎት የሚችሉ ጉዳዮችን መጠቀም

1 thought on “የረውማቲክ የልብ በሽታ እንዳይባባስ የሚረዳውን በመርፌ የሚሰጥ ህክምና (ቤንዛቲን ፔኒሲሊን)”

  1. I can’t get the medication on the market , I think it is disappeared.

    Please inform me where I can get it . Thank you .

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *