የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ለልብ ሕሙማን

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ትላንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ማዕከላችን የሚሰጠውን የነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በዘላቂነት ለመደገፍ የታክስ የዕዳ ምህረትና ከኪራይ ገቢ ግብር ነፃ እንዲደረግ ወስኗል፡፡ የከተማችን ም/ከትንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ካቢኔያቸው የነፍስ አድን ስራውን በዘላቂነት ለማስቀጠል እንችል ዘንድ ላደረጉልን አዎንታዊ ሚና ያለው ድጋፍ በታካሚ ሕፃናቱ ስም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ #OfficeoftheMayorAddisAbaba | …

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ለልብ ሕሙማን Read More »

አስኩ ኃላ.የተ.የግ.ማ (ASKU P.L.C.) ለልብ ማዕከል የመፅሀፍት ድጋፍ አደረገ

በአኳ አዲስ ምርቱ እና በተለያዩ ዘርፈ ብዙ የንግድ እንቅስቃሴዎች የሚታወቀው አስኩ ኃላ.የተ.የግ.ማ (ASKU P.L.C.) የልብ ሕሙማንን ለረጅም ዓመታት በተለያዩ መንገዶች ሲደግፍ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በማዕከላችን ውስጥ ለተቋቋመው ቤተ መፅሀፍት 306 መፅሀፍቶችን አበርክቷል፡፡ የቤተ መፅሀፍቱ መቋቋም የሕክምና ባለሞያዎች ለሚያደርጉት የዕውቀት ማዳበር እና ሽግግር፣ በማዕከሉ ሰራተኞች ዘንድ የንባብ ልምድን ለማዳበር እና በዋነኛነት በማዕከላችን ለሚታከሙ ሕፃናት የንባብ …

አስኩ ኃላ.የተ.የግ.ማ (ASKU P.L.C.) ለልብ ማዕከል የመፅሀፍት ድጋፍ አደረገ Read More »

ኢትዮ ቴሌኮም እና የልብ ሕሙማን

የረጅም ጊዜ አጋራችን የሆነው #ኢትዮ_ቴሌኮም ዛሬም እንደሁልጊዜው የድጋፍ ጥሪያችንን ተቀብሎ አስተናግዶናል፡፡ ላለፉት በርካታ ዓመታት በተለያዩ መንገዶች ማዕከላችንን ለመደገፍ በሩን ክፍት አድርጎ የሚጠብቀን #ኢትዮ_ቴለኮም የ6710 ዓጭር የፅሁፍ መልዕክት በነፃ በመፍቀድ፣ የ30ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ስፖንሰር በማድረግ እንዲሁም ለሚያጋጥሙን የኮሚኒኬሽን ችግሮች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ማዕከላችን ለሚያከናውናቸው የሕይወት ማዳን ስራዎች ትልቅ ሚና ተጫውቷል በመጫወት ላይም ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም …

ኢትዮ ቴሌኮም እና የልብ ሕሙማን Read More »

የሜሎሪና ደራሲ ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ በልብ ማዕከል

ወጣቱ ደራሲ ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ ዛሬ በማዕከላችን በመገኘት በቅርቡ ያሳተመውን “ሜሎሪና” የተሰኘ የበኩር መፅሀፉን ዕትሞች እና የ15 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጎልናል፡፡ ልብ የሚሹ ሕፃናትን ለመደገፍ ካለህ ላይ ስላበረከትክልን ከልብ እናመሰግንሀለን፡፡ #nahusenaytsedaluabera | #CHFE | #CCE#6710_A_B_C_D

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ እና People To People

ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ እና People To People በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።በበይነመረብ ላይ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ (Virtual Meeting) የPeople To People መስራች ፕ/ር እናውጋው መሀሪ እና ሌሎች አባላት፣ ክቡር አምባሳደር ፍፁም አረጋ፣ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ ከሌሎች የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ተወካዮች ጋር እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፎ አድርገዋል። ውይይቱ ወቅታዊ የልብ …

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ እና People To People Read More »

ሆራ ትሬዲንግ ለልብ ማዕከል በኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

15ኛ የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘው ሆራ ትሬዲንግ ባሳለፍነው ሳምንት በልብ ማዕከላችን በመገኘት የ አንድ ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድርጅቶች ከተቋቋሙበት አላማ በተጨማሪ ማሕበረሰባዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ትልቅ ማሳያ የሆነ ተግባር በመፈፀማችሁ እና በርካታ ሕፃናት እንዲድኑ ትልቅ አስተዋፅዖ በማድረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

ጳጉሜን በምስጋና

በዓመቱ ውስጥ የልብ ማዕከላችንን በመደገፍ የበርካታ ሕፃናት ሕይወት እንዲድን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላደረጉ አጋሮቻችን ምስጋናችንን አቅርበናል፡፡ ልበ ቀና ሆናችሁ የተሰበሩ ልቦችን እንድንጠግን ላገዛችሁን ሁሉ ምስጋናችን ከልብ ነው፡፡ በምስጋናችን ወቅት ያስቀረናቸውን ምስሎች እነሆ፡፡

ልጅ ቧያለው ጌታቸው አባተ

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ መስራችና ከቦርድ አባላት አንዱ የነበሩት እና የህይወት ዘመን አባል የሆኑት #ልጅ_ቧያለው_ጌታቸው_አባተ ባሳለፍነው ሳምንት ከባለቤታቸው #ወሮ_ማንያህልሻል_አንተነህ ጋር በመሆን ማዕከላችንን በመጎብኘት የሕይወት ማዳን ስራው እንዲቀጥል አሁንም አብረናችሁ ነን ብለውናል፡፡ ልጅ ቧያለው በጉብኝታቸው ወቅት በአያታቸው #ራስ_አባተ_ቧያለው_ንጉሡ (አባ ይትረፍ) ህይወት ዙሪያ የታተመውን መፅሐፍ ለማዕከላችን በስጦታ መልክ ያበረከቱ ሲሆን መፅሀፉ አባትና አያቶቻችን ሀገር ለመገንባትና ለእኛ ለማውረስ ያደረጉትን ጥረትና የከፈሉትን መስዋትነት የሚያሳይ …

ልጅ ቧያለው ጌታቸው አባተ Read More »

UNECA at Cardiac Center Ethiopia

What a delight it was for all of us here at Cardiac Center Ethiopia to have her excellency Vera Songwe, Executive Secretary of UNECA, and staff representatives of the Economic Commission for Africa.Thank you for your generous donation of 800,000 ETB to mend broken hearts. #UNECA#Cardiac_Center_Ethiopia#6710_A_B_C_D

የሳውዝ ዌስት አካዳሚ Charity Club ለልብ ማዕከል በኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ሳውዝ ዌስት አካዳሚ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ባቋቋመው የCharity Club አማካኝነት ድጋፍ ለሚሹ ማዕከላትና ግለሰቦች በየአመቱ የሚከናወኑ የተለያዪ ድጋፎችን በመስጠት ማሕበረሰባዊ ሀላፊነቱን በመወጣት ላይ የሚገኝ ትምህርት ቤት ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ከያዛቸው ዕቅዶች አንዱ የሆነውን የ200,000 ብር እርዳታ ለልብ ማዕከላችን አበርክቷል፡፡ ታዳጊ ሕፃናትን በትምህርት አንፆ ከማሳደግ ተልዕኳችሁ በተጨማሪ የልብ ሕመምተኛ የሆኑ ሕፃናትን ህይወት ለማዳን በሚደረገው እርብርብም ላይ …

የሳውዝ ዌስት አካዳሚ Charity Club ለልብ ማዕከል በኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ Read More »

3D printed face shields donated by the Israeli Embassy

Following the outbreak of the Coronavirus pandemic (COVID-19) worldwide, the Israeli Embassy in Ethiopia donated 3D printed 220 face shields to Cardiac Center Ethiopia (CCE) in Addis Ababa, for the use of its medical staff. We are very grateful for the donation and all the support from the embassy on fighting COVID-19 and saving children’s …

3D printed face shields donated by the Israeli Embassy Read More »

Meet Alene/አለነን ተዋወቁት

አለነ የሺዋስ የ17 አመት ወጣት ሲሆን ተዳጋጋሚ የጉሮሮ ኢንፌክሽንን ተከትሎ በሚከሰት የልብ ሕመም ከአራቱ የልብ በሮች ሁለቱ በከፍተኛ ሁኔታ በመጎዳታቸው ለረጅም ጊዜ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ስላገደው ትምህርቱን ከሶስተኛ ክፍል ለማቋረጥ ተገዶ ቆይቷል፡፡ በልብ ማዕከል በኢትዮጵያ ላለፉት 3 ዓመታት ወረፋ በመጠበቅ፤ ባሳለፍነው ሳምንት በተደረገለት ቀዶ ሕክምና ወደ ሙሉ ጤንነቱ መመለስ ችሏል፡፡