በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ እና People To People

ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ እና People To People በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።በበይነመረብ ላይ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ (Virtual Meeting) የPeople To People መስራች ፕ/ር እናውጋው መሀሪ እና ሌሎች አባላት፣ ክቡር አምባሳደር ፍፁም አረጋ፣ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ ከሌሎች የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ተወካዮች ጋር እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፎ አድርገዋል። ውይይቱ ወቅታዊ የልብ …

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ እና People To People Read More »

ሆራ ትሬዲንግ ለልብ ማዕከል በኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

15ኛ የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘው ሆራ ትሬዲንግ ባሳለፍነው ሳምንት በልብ ማዕከላችን በመገኘት የ አንድ ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድርጅቶች ከተቋቋሙበት አላማ በተጨማሪ ማሕበረሰባዊ ኃላፊነትን ለመወጣት ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ትልቅ ማሳያ የሆነ ተግባር በመፈፀማችሁ እና በርካታ ሕፃናት እንዲድኑ ትልቅ አስተዋፅዖ በማድረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

ጳጉሜን በምስጋና

በዓመቱ ውስጥ የልብ ማዕከላችንን በመደገፍ የበርካታ ሕፃናት ሕይወት እንዲድን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላደረጉ አጋሮቻችን ምስጋናችንን አቅርበናል፡፡ ልበ ቀና ሆናችሁ የተሰበሩ ልቦችን እንድንጠግን ላገዛችሁን ሁሉ ምስጋናችን ከልብ ነው፡፡ በምስጋናችን ወቅት ያስቀረናቸውን ምስሎች እነሆ፡፡

ልጅ ቧያለው ጌታቸው አባተ

በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ መስራችና ከቦርድ አባላት አንዱ የነበሩት እና የህይወት ዘመን አባል የሆኑት #ልጅ_ቧያለው_ጌታቸው_አባተ ባሳለፍነው ሳምንት ከባለቤታቸው #ወሮ_ማንያህልሻል_አንተነህ ጋር በመሆን ማዕከላችንን በመጎብኘት የሕይወት ማዳን ስራው እንዲቀጥል አሁንም አብረናችሁ ነን ብለውናል፡፡ ልጅ ቧያለው በጉብኝታቸው ወቅት በአያታቸው #ራስ_አባተ_ቧያለው_ንጉሡ (አባ ይትረፍ) ህይወት ዙሪያ የታተመውን መፅሐፍ ለማዕከላችን በስጦታ መልክ ያበረከቱ ሲሆን መፅሀፉ አባትና አያቶቻችን ሀገር ለመገንባትና ለእኛ ለማውረስ ያደረጉትን ጥረትና የከፈሉትን መስዋትነት የሚያሳይ …

ልጅ ቧያለው ጌታቸው አባተ Read More »