በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ እና People To People

ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ እና People To People በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።በበይነመረብ ላይ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ (Virtual Meeting) የPeople To People መስራች ፕ/ር እናውጋው መሀሪ እና ሌሎች አባላት፣ ክቡር አምባሳደር ፍፁም አረጋ፣ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ ከሌሎች የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ተወካዮች ጋር እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፎ አድርገዋል።

ውይይቱ ወቅታዊ የልብ ማዕከል እንቅስቃሴን በመቃኘት የተጀመረ ሲሆን #ዘላቂ_የሆነ_ፋይናንሺያል_አቅም_መፍጠርን#የምርምር_እና_ትምህርት_ግንኙነቶች_ማዘጋጀትን#የገቢ_ማሰባሰቢያ_ዝግጅቶች_ማቀድን#በቂ_የአላቂ_እቃ_አቅርቦት_ማግኘት_የሚቻልባቸው_እንቅስቃሴዎች_ማድረግ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።ውይይቱ ሁሉም ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን አቅርበው እና መጀመር ስላለባቸው እንቅስቃሴዎች ስምምነት ላይ ተደርሶ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

ይህ ግንኙነት ለድርጅታችን ትልቅ ተስፋ ሰጪ ጅምር ነውና ዕቅዶችን ወደ ተግባር በመቀየር የበርካታ የኢትዮጵያ ሕፃናትን ህይወት መታደግ እንደምንችል ባለሙሉ ተስፋ እና ቁርጠኛ መሆናችንን እየገለፅን ለPeople To People እና በውይይቱ ተሳታፊ ለነበራችሁ ሁሉ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

A historical zoom meeting was held last week on creating a partnership between The Children’s Heart Fund of Ethiopia and People to People to achieve the sustainability vision of the center.

The founder of People To People Prof. Enawgaw Mehari with his colleagues, H.E. Ambassador Fitsum Arega, Pro. Afework Kassu with other CHFE/CCE representatives and invited guests attended the virtual meeting.

Among different topics discussed, creating a sustainable financial stand, building academic and research relations, developing fund raising programs, finding out ways to have sufficient consumables and other related issues were addressed in detail.

We believe this kind of relation is essential for our current activities and accomplishing our goals in the long term. We are very grateful to have you by our side and thank you all for attending the meeting.

#peopletopeople | #CHFE | #cardiaccenterethiopia

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *