የልብ ሕመምና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ

(በዶ/ር አዘነ ደሴ መንግስቱ፤ በልብ ማዕከል የህፃናት የልብ ሐኪም)

1. በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወይም ውድድር ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉና የልብ ህመም መኖርን ጠቋሚ ምልክቶች (warning signs) ምንድንናቸው?

  • ያልተለመደ የድካም ስሜት መኖርና ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ከአጭር ጊዜ በኋላ መቀጠል ለመቻል
  • የደረት ውጋት
  • ራንን መሳት (syncope)
  • የማዞር ስሜት (dizziness)
  • የልብ ምት ጎልቶና በፍጥነት ለራስ መሰማት (palpitation)

2. በውድድርና ጠንከር ባለ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወይም ልምምድ ወቅት በልብ ህሙማን ሕይወት ላይ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ የልብ ደዌዎች (በሽታዎች) የትኞቹ ናቸው?
  • በአብዛኛው በዘር የሚተላለፍና የልብ ውስጥ ጡንቻ ባልተፈለገ መልክ መወፈር
  • ከልብ የግራ የታችኛው ክፍል የሚወጣው የደም ቧንቧ መነሻ ላይ የሚከሰት ከፍተኛ ጥበት
  • የተዛባ የልብ የኤሌክትሪክ አሠራር
  • ለልባችን የተስተካከለ አሠራር ኦክስጅን የሚያቀብሉ የደም ማሰራጫዎች (coronary arteries) ላይ ችግር መኖር
  • በልብ ውስጥ ፔስ ሜከር ወይም ሌላ የልብን አሠራር የሚደግፍ መሣሪያ መኖር (እነዚህ ሰዎች ግጭትን ከሚፈጥር ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማቀብ አለባቸው)

 3. በተፈጥሮ የሚከሰት የልብ ሕመም ያለባቸው ሕፃናትና አዋቂዎች ስፖርታዊ እንቅሰቃሴ ማድረግ ይችላሉ?

  • በተራ ቁጥር ሁለት ከተጠቀሱት የልብ ደዌዎች ካለባቸው ውጭ አብዛኞቹ የተፈጥሮ የልብ ሕሙማን መለስተኛና መካከለኛ ስፖርታዊ እንቀስቃሴ ያለገደብ ማድረግ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ስፖርታዊ እንቅስቃሴን በሚመለከት በሚከታተላቸው የልብ ሐኪም የተለየ ትዕዛዝ (exercise prescription) ካልተሰጠ በስተቀር በተለይ የልብ ሕሙማን ሕፃናትን ከአቻዎቻቸው ጋር እንዳይጫወቱ መገደብ ተገቢ አይደለም፡፡
  • የተፈጥሮ የልብ ችግሩ ውጤታማ በሆነ መንገድ በኦፕራሲዮን ወይም በሌላ ዘዴ የተስተካከለላቸው ህሙማን ችግሩ ከተከሰተ ከ3-6 ወር ጀምሮ የሚከታተላቸውን የልብ ሐኪም ካማከሩ በኋላ ያለገደብ እንቅስቃዎችን ማድረግ ይችላሉ፡፡

4. ተፈጥሮአዊም ሆነ ሰዎች ከተወለዱ በኋላ በሂደት የሚያጋጥም የልብ ሕመም ያለባቸው ሰዎች አትሌት ለመሆን ከፈለጉ ከውሳኔያቸው በፊት ምን ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?

  • ልምምድ ሲጀምሩ በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱት አደገኛ ምልክቶች (warning Signs) አለመኖራችን ማስተዋልና ምልክቶችን ካዩ የልብ ሐኪምን ማማከር
  • ከዚህ በፊት በልብ ሐኪም የተረጋገጠ የልብ ሕመም ካለ የሚከታተላቸውን ባለሙያ ማማከርና አስፈላጊውን ቅድመ ምርመራ (sports preparticipation screening) በማድረግ ብቁ መሆንን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *